ለሕይወትዎ አስቸጋሪ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይፈልጋሉ? ይህ ድህረ-ገፅ የተዘጋጀዉ መልሶችን ለማግኘት እንዲችሉ እርስዎን ለመርዳት ነዉ፡፡ ይህ ዓለምን የመድረስ አገልግሎት ከ175 በላይ በሆኑ አገሮች ዉስጥና ከ120 በሚበልጡ የተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርቶችን ይሰጣል፡፡
አብዛኞቹ ትምህርቶች በህትመት መልክ ተዘጋጅተዉ የቀረቡ ናቸዉ፡፡ የሚፈልጉትን ያህል ኮፒ አድርገዉ እንዲገለገሉ ተፈቅዶልዎታል፡፡ በቪዲዮ እና በኦዲዮ የተዘጋጁ ትምህርቶችም አሉ፡፡
ከነዚህ ኮርሶች መካከል አንዳዶች ስለህይወት አበይት ጥያቄዎች፣ ስለሕይወት ዓላማና ሰዉ ከሞት በኋላ ስለሚጠብቀዉ ነገር የሚዳስሱ ናቸዉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ጋብቻን፣ ቤተሰብን፣ስነምግባርንና ማህበረሰብን በሚመለከት የተዘጋጁ ናቸዉ፡፡
የግሎባልሪች አገልግሎት እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚረዱ፣ የክርስትናን ህይወት መኖርና ሌሎችን ማገልገል እንዲችሉ የሚያዘጋጁ ኮርሶችን አቅርቦልዎታል፡፡ ኮርሶቹም በነፃ የሚሰጡ ናቸዉ፡፡ ሌሎች አዳዲስ ኮርሶችንና በሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች የሚቀርቡ ትምህርቶችን እንዲያገኙ አዘዉትረዉ ይጎብኙን፡፡