Help

የምትምህርቶች አከፋፈትና የማተም ዘዴ

በዚህ ድህረ ገፅ ላይ የሚገኙት ኮርሶች በፒዲኤፍ(PDF)ፋይል የቀረቡ ናቸዉ፡፡ ይህ መሆኑ ኮርሶችን በቀላሉ ከፍተዉ እንዲያዩ፣ ኮምፒተርዎ ላይ ማስቀረት እንዲችሉና ከኮምፒተርዎ ማተም እንዲችሉ ይረዳል፡፡ ትክክለኛዉ ሶፍትዌር ኮምፒተርዎ ላይ ተጭኖ ከሆነ(ከዚህ በታች ይመልከቱ) እነዚህን ትምህርቶች ከፍተዉ ማንበብ፣ ኮምፒዉተርዎ ላይ ማስቀረትና ማተም ይችላሉ፡፡

እነዚህን ትምህርቶች ከፍቶ ለማንበብ፣ ኮምፒዉተርዎ ላይ ለማስቀረትና ለማተም አዶቤ አክሮባት ሪደርን (Adobe Acrobat Reader® 6.0 ) ወይም በቅርብ የወጣዉን ማንበቢያ ኮምፒዉተርዎ ላይ መጫን አለብዎ፡፡ ከ Adobe.com® ድህረ ገፅ ኮምፒዉተርዎ ላይ መጫን ይችላሉ፡፡

በኦዲዮ ለመስማት

በኦዲዮ ተዘጋጅተዉ የቀረቡ ትምህርቶችን ለማድመጥ «ኦዲዮ ለመስማት» የሚለዉን አገናኝ ርዕስ ይጫኑ ፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችልዎ ሶፍት ዌር ኮምፒተርዎ ላይ በትክክል ተጭኖ ከሆነ(ከዚህ በታች ይመልከቱ) ወዲያዉኑ ከፍቶ ማጫወት ይጀምራል፡፡
ትምህርቶችን በኦዲዮ ለመስማት በቅርብ ተሻሽሎ የወጣ ሪያል (RealPlayer )ኮምፒዉተርዎ ላይ መኖር አለበት፡፡ ይህን ደግሞ ከሪያል ኔትዎርክ ድህረገፅ RealPlayer ኮምፒዉተርዎ ላይ መጫን ይችላሉ፡፡

ቪዲዮ ለመመልከት

በቪዲዮ ተዘጋጅተዉ የቀረቡ ትምህርቶችን ለመመልከት «ቪዲዮ ይመልከቱ» የሚለዉን አገናኝ ርዕስ ይጫኑ፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችል ሶፍት ዌር ኮምፒተርዎ ላይ በትክክል ተጭኖ ከሆነ (ከዚህ በታች ይመልከቱ) ወዲያዉኑ ከፍቶ ማጫወት ይጀምራል፡፡
ትምህርቶችን በቪዲዮ ለማየት የሚያስችል በቅርብ ተሻሽሎ የወጣ ሪያል (RealPlayer )ማጫዎቻ ኮምፒዉተርዎ ላይ መኖር አለበት፡፡ ከሪያል ኔትዎርክ ድህረገፅ RealPlayer ኮምፒዉተርዎ ላይ መጫን ይችላሉ፡